Amharic
የሴቶች መረጃና ለተገቢ አገልኢሎት ሰጭ ማስተላለፍ ፤ዊር (WIRE) ምንድን ነው?
የሴቶች መረጃ እና ለተገቢ እርዳታ ማስተላለፍ ዊር (WIRE) ለሴቶች በሴቶች የሚመራ በቪክቶሪያ የሚገኝ ድርጅት ነው። ዊር (WIRE) ነጻ፡ በሚስጢር የተጠበቀ መረጃ ፡ ደጋፍና ለሴቶች በስልክ እርዳታ ማሰተላለፍ እርዳታን በበሜልበር ከተማ መካከል በሚገኘው የሴቶች መረጃ ማእከል አማካይነት ይሰጣል።
በማንኛውም እድሜ ክልል ያሉ ሴቶች ስለማንኛውም ትንሽም ሆነ ትልቅ ችግር በተመለከተ ዊርን (WIRE) ማነጋገር ይችላሉ። የሴት ሐኪም፣ ጠበቃ ወይንም አማካሪ ለማግኘት ልንረዳዎ እንችላለን። የማህበረሰብ ወይም የግል ደህንነትን፡ ስራ ማፈላለግ አገልግሎት ሰጭዎችን ፡እንደ የማህበረሰብ ጤንነት አገልግሎት ማእከል፡የመኖሪያ ቤት ፡ ስራ ማፈላለግ አገለግሎቶችን የመሳሰሉትን የሚፈልጉ ከሆነ ልንረዳዎ እንችላለን።
የዊር (WIRE) ስልክ ቁጥር
በስልክ ቁጥር 1300 134 130 ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 3፡00 (9:00am) ሰዓት እስከ ምሽቱ 11፡00 (5:00pm) ሰዓት ከማንኛውም የቪክቶረያ አካባቢ ሆነው መደበኛውን የስልክ ክፍያ በቻ በመክፈል መደወል ይችላሉ። (ከሞባይል ስልክ ሲደውሉ እንደማንኛውም የሞባይል ዋጋ ያስከፍሎታል)።
የመስማት ችግር ከአለብዎት በብሔራዊ ተዘዋዋሪ 13 36 77 TTY ይደውሉ።
አሰተርጓማዊዎች ይኖራሉ
ዊር (WIRE)ን በእራስዎ ቋንቋ ማናገር ከመረጡ የስልክ አሰተርጓሚ አገልገሎት አለን። በሚደውሉበት ጊዜ አስተርጋሚ እንዲቀርብሎት ይጠይቁ። ስምዎንና ስልክቁጥሮን በመውሰድ የእርስዎን ቋንቋ የሚያስተረጉም ሰው እንደ አገኘን መልሰን እንደውልሎታለን።
ዊርን (WIRE) ስለ ምን ማናጋገር ይችላሉ?
- በቤት ውስጥ ሰለ አልዎት ችግር
- ሰለጤናና የግል ደህንነትዎ
- የህግ አማካሪ እንዴት እንደሚያገኙ
- ሥራ ስለማግኘት ፡ ስልጤና ወይም የትምህርት አማራጮች ፣ ንግድ ስለመጀመር
- የሚኖሩበት ስፍራ ሰለማፈላለግ
- ሰለ ገንዘብ ችግር
- በትምህርት ቤት ሰለአለብዎት ችግር
- በስራ ቦታ ስለ አለብዎት ችግር
- በማህበረስቡ ውስጥ ያሎትን ተሳትፎ ሰለመጨመር
- በአጠቃላይ ሰለማንኛውም ነገር
ምንም አይነት መረጃ ማግኘት ካስፈለግዎት ሁልጊዜም መነሻዎ ከዊር ቢሆን ጥሩ ጅምር ይሆናል።
ዊርን (WIRE) በሚያነጋገሩበት ጊዜ ምንድነው የሚሆነው?
ባለሙያና ያሉበትን ሁኔታ መረዳት የምትችልና ሰዎችን መርዳት የምትችል የእርስዎን ሚስጥር የምትጠብቅ ሴት ያናጋግራሉ። ሰራተኞቻችንና ያለክፍያ በስልክ አገልገሎት ሰጭዎች ህይወት ዘመናቸው ያከበቱት ሰፊና የጠለቀ ልምድ ያላቸው ፣ ከተለያዩ አገሮች የመጡ፣ የተለያየ ልምድ ያላቸውና ስልጠናቸውን በሚገባ ያጠናቀቁ ናቸው።
የሴቶች መርጃ ማዕከልን ይጎብኙ
ወደ ማዕከሉ ለመምጣት ምንም አይነት ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግም ምንጊዜም በመምጣት፡
- በአካል ፊት ለፊት ተገኝቶ እርዳታ ማግኝት ፣ መረጃና ወደሚመለከተው የእርዳታ ሰጭ አገልግሎት መመራት
- የተለያዩ ርዕሶችን ከጤና እስከ ህጋዊ መብት በተመለከተ መረጃ
- ነፃ ኮምፒተር፡ የእንተርኔትና የጻፉትን ማተም
- የነፃ የኮምፒተር ትምህርትና የሥራ ማፈላለግ ክለብ
- የሥራ ፍለጋ፣ ወደ ትምህርት መመለስን ወይንም በኢንተርኔት ሥራ ማፈለለግ እርዳታ
- አረፍ ለማለት ፣ ህፃን ለመመገብ ወይም ወግ ለማውጋት ለመሳሰሉት ሁል እርዳታ ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻችን
Ground Floor, Queen Victoria Women’s Centre
210 Lonsdale Street, Melbourne
(between Swanston Street and Russell Street)
የሥራ ሠዓታችን
ከጠዋቱ 4፡30 (10.30am) አስከ ምሽቱ 11፡00 (5.00pm) ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ
ኢሜል አድራሻ
መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በኢሜል አድራሻችን inforequest@wire.org.au በእንግሊዘኛ ሊጠይቁን ይችላሉ።
ድህረ ገፃችንን ይጎብኙ
www.wire.org.au በመመልከት መረጃዎችን የዊርን (wire) ነፃ ተከታታይ ሴሚናሮችን እንዲሁም ጠቃሚ ሌሎች ጠቃሚ ድረ ገጾችን ያገኛሉ።
